ዜናዎች እና ክስተቶች

ዜናዎች

“የኅብረት ሥራ ማህበራት ሚና ለኢትዮጵያ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል ከጥር 28 እስከ የካቲት 3/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማእከል የሚካሄድ ባዘርና የሚሲንፖዚየም ተከፈተ።

ጥር 28/05/2017 “የህብረት ሥራ ማህበራት ሚና ለኢትዮጵያ ብልጽግና”  በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ ህብረት ሥራ ኮሚሽን እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ህብረት ሥራ ኮሚሽን በጋራ ያዘጋጁት የኅብረት ሥራ ማኅበራት ኤግዚቢሽን ባዘርና ሲምፖዚየም ተከፍቷል፡፡ የኤግዚቢሽን፤ ባዛርና ሲምፖዚየሙ ከጥር 28 እስከ የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም ለ5 ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን ማህበራችን ሸገር የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/መሰ/ኀ/ስ/ማ በዚሁ ኤግዚቢሽን ባዘርና ሲምፖዚየም ላይ በመሳተፍ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በእግዚቢሽንና ባዛሩ ለሚሳተፉ የህብረተሰብ ክፍሎች በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል፡፡

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለከተራ በዓል እና ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ፡፡ በዓሉ የሰላም፣ የአብሮነት እና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን፡፡ ሸገር የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኅ/የተ/መ/ኅ/ሥ/ማኅበር ይቆጥቡ ይበደሩ በጋራ እንችላለን!!!
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዓሉ የሰላም፣ የአብሮነት እና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ ከልብ እየተመኘን የመደበኛ ቁጠባዎትን ሳያቋርጡ እንዲቆጥቡ ለማስታወስ እንወዳለን መልካም የገና በዓል ይሁንልዎ።

ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር መሰረታዊ የህብረት ስራ ማህበር ከአሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር መሰረታዊ የህብረት ስራ ማህበር ጋር የልምድ ልውውጥ አካሄደ፡፡      ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ( ታሀሳስ 16 ቀን 2017ዓ.ም)

የሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር  መሰረታዊ የህብረት ስራ ማህበር የማኔጅመንት አባላት፣ከፍተኛ ባለሙያዎችና የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች  በአሚጎስ የገንዘብ ቁጠባ ብድር  መሰረታዊ የህብረት ስራ ማህበር ቢሮ በመገኘት የልምድ ልውውጥ አድርገዋል፡፡ የልምድ ልውውጡ ዋና ትኩረት የተቋሙን የሰው ሀይል አደረጃጀት፣ የፋይናንስ አሰራር፣ ድጅታል አሰራር፣ የስጋት ትንበያ አስተዳደር፣ የአባላት አያያዝና እርካታ እና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ ሲሆን የተቋሙ ትምህርትና ስልጠን ክፍል ሃላፊ የሆኑት አቶ ሀጎስ እና የፕላንና በጀት ክፍል ሃላፊ የሆኑት አቶ ሳምሶን በተገኙበት አጠቃላይ ስለተቋማቸው አሰራርና ከላይ በተጠቀሱት ርእሰ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ የሆነ ገለጻ የተደረገ ሲሆን  በቀጣይ በየስራ ክፍል ራሱን ችሎ ልምድ ልውውጥ እንደሚኖር በመግባባት እና የአሚጎስን የቢሮ አደረጃጀት በመጎብኘት የእለቱን ልምድ ልውውጥ አጠናቀናል ፡፡

በጋራ እንችላለን!!!!!!!!

ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር እና  አሐዱ ባንክ አክሲዮን ማኅበር በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡ 

የስምምነቱ መሰረታዊ ዓላማ የፋይናንስ ተደራሽነትን የተሻለ ለማድረግ፣ የፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ትብብር ለመፍጠርና በአጠቃላይ  ቁጠባን በማበረታታት ሀብት ለማሰባሰብና የብድር ፍላጎትን ለማሟላት ታሳቢ ያደረገ ነው::እንደሚታወቀው አሐዱ ባንክ ከብድር የእቅድ በጀቱ ላይ 15℅ የሚሆነውን ለታችኛው የኅብረተሰብ ክፍል ለማበደር ቁርጠኝነቱ አለው:: በመሆኑም ይህ ስምምነት ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ በተመረጡት የትብብር ማዕቀፎች ላይ በጋራ የሚሰራ ይሆናል:: 

ነሐሴ 30/ 2015 ዓ.ም

አዲስ አበባ~ ኢትዮጵያ

ክስተቶች/Events

ሸገር የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር 3ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ

ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/መሰ/ኅብረት ሥራ ማኅበር  ነሐሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም በአባላት ተወካዮች አማካኝነት 3ተኛ መደበኛ ጉባኤውን በካፒታል ሆቴል በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል::

በእለቱ በቀረቡ አጀንዳዎች ማለትም:-

1. የ2014 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ማዳማጥና ውሳኔ ማሳለፍ
2. የቁጥጥር ኮሚቴ ሪፖርት ማዳመጥና ውሳኔ ማሳለፍ
3. የ5 ዓመት ስትራቴጅክ እቅድ ዝግጅት ማዳመጥና ውሳኔ ማሳለፍ
4. የ2015 በጀት ዓመት እቅድ ዝግጅት ማዳመጥና ውሳኔ ማሳለፍ
5. በመተዳደሪያ ደንብና በብድር መመሪያው ላይ የማሻሻያ አንቀጾችን አዳምጦ ውሳኔ ማሳለፍ በሚሉት አጀንዳዎች ላይ ጉባኤተኛው ተወያይቶ ጠቃሚ ውሳኔዎችን አሳልፏል:: ከአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ማደራጃ የተወኩሉ አካላት በእለቱ ተገኝተው ለሸገር ጠቃሚ የሚሆኑ ሃሳቦችን ሰጥተዋል:: ሸገር እስከዚህ ወር ድረስ 47 ሚሊዮን ብር ካፒታልና 1832 አባላት አለው:: ይህ አፈፃፀም የአንድ ዓመት ከአምስት ወር ሥራ ውጤት ነው::

በጋራ እንችላለን!!!

ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር /የተ/መሰ/ኅብረት ሥራ ማኅበር 6ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ !!

ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር /የተ/መሰ/ኅብረት ሥራ ማኅበር በቀን 27/11/2016 . አባላት እና ተወካዮች በተገኙበት 6ተኛ መደበኛ ጉባኤውን በኢትዮጵያ ሆቴል በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል::

በእለቱ በቀረቡት

1.የህብረት ስራ ማህበሩን 2016 በጀት ዓመት የተከናዎኑ ተግባራትን ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ ማፅደቅ።

2. የህብረት ስራ ማህበሩን 2016 በጀት ዓመት  የቁጥጥር ኮሚቴ ሪፖርት ማዳመጥ፦

3 .የህብረት ስራ ማህበሩን 2017 በጀት ዓመት  እቅድ ማዳመጥና ተወያይቶ ማፅደቅ

4. የተለያዩ የብድር መመሪያ ማሻሻያዎች ማቅረብና ተወያይቶ ማፅደቅ

5. በህብረት ስራ ማህበሩ አባላት በማፍራት፣ብድር ወስዶ በወቅቱ በመመለስ እና ሳያቆራርጡ ለቆጠቡ አባላት የምስጋና ወረቀት መስጠት በሚሉት አጀንዳዎች ላይ ጉባኤተኛው በሰፊው ተወያይቶ ጠቃሚ ውሳኔዎችን አሳልፏል::

ከእነዚህ መካከል ያለውን የገንዘብ የመግዛት አቅምና የገበያ ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት

Ø  ለንግድ ጉዳይ እስከ1,000,000.00 የነበረው ወደ 1,200,000 ከፍ እንዲል

Ø  ለመኪና እስከ 2,000,000.00 የነበረው ወደ 2,500,000.00 ከፍ እንዲል

Ø  ለቤት 3,000,000.00 የነበረው ወደ 4,000,000.00 ከፍ እንዲል በጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ ተላልፏል::

Ø  ከዚህ በተጨማሪ የአጭር ጊዜ የብድር አማራጮች ምክረ ሃሳብ በአመራሩ ቀርቦ በጠቅላላ ጉባኤው ይሁንታን አግኝቷል::

  በዕለቱም ከአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ማደራጃ የተወኩሉ አካላት  ተገኝተዋል። በውይይቱም አባላት ለሸገር ኅብረት ሥራ ማኅበር ማደግ የሚበጁ ጠቃሚ ምክረ ሀሳቦችን በመስጠት ለህብረት ስራ ማህበራችን  ግብዓት ሰጥተዋል። ጉባኤውም በውጤታማነት  እንዲጠናቀቅ ትልቅ ሚና ነበራቸው።

ሸገር  እስከዚህ ወር ድረስ 171 ሚሊዮን ብር ብድር ለአባላቱ የሰጠና 4703 በላይ የአባላት ቁጥር መድረሱን ለማወቅ ተችሏል::

አቶ ቁምነገር ማስረሻ የሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/መሰ/ኅብረት ሥራ ማኅበር ዋና ሰብሳቢ
ከአዲስ አበባ ሕብረት ስራ ኤጀንሲ ስለ ጠቅላላ ጉባኤው አስተያየት ሲሰጡ
አቶ በላይነው አሻግሬ የቁጥጥር ኮሚቴ ሰብሳቢ ሪፖርት ሲያቀርቡ
ለቀረቡ ሪፖርቶች፤ መመሪያዎች እና ማሻሻያዎች አባላት ሲያፀድቁ
የሸገር የገ/ቁ/ብ/ኃ/የተ/መሰ/ኅብረት ሥራ ማኅበር አመራሮች ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ
አባላት ማበረታቻ የምስክር ወረቀት ዕውቅና አሰጣጥ ፕሮገራም
አቶ ባንተግዜ አምባው የሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/መሰ/ኅብረት ሥራ ማኅበር ምክትል ሰብሳቢ ሽልማት ሲሰጡ