ዜናዎች እና ክስተቶች

ዜናዎች

ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር እና  አሐዱ ባንክ አክሲዮን ማኅበር በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡ 

የስምምነቱ መሰረታዊ ዓላማ የፋይናንስ ተደራሽነትን የተሻለ ለማድረግ፣ የፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ትብብር ለመፍጠርና በአጠቃላይ  ቁጠባን በማበረታታት ሀብት ለማሰባሰብና የብድር ፍላጎትን ለማሟላት ታሳቢ ያደረገ ነው::እንደሚታወቀው አሐዱ ባንክ ከብድር የእቅድ በጀቱ ላይ 15℅ የሚሆነውን ለታችኛው የኅብረተሰብ ክፍል ለማበደር ቁርጠኝነቱ አለው:: በመሆኑም ይህ ስምምነት ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ በተመረጡት የትብብር ማዕቀፎች ላይ በጋራ የሚሰራ ይሆናል:: 

ነሐሴ 30/ 2015 ዓ.ም

አዲስ አበባ~ ኢትዮጵያ

ክስተቶች/Events

ሸገር የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር 3ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ

ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/መሰ/ኅብረት ሥራ ማኅበር  ነሐሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም በአባላት ተወካዮች አማካኝነት 3ተኛ መደበኛ ጉባኤውን በካፒታል ሆቴል በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል::

በእለቱ በቀረቡ አጀንዳዎች ማለትም:-

1. የ2014 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ማዳማጥና ውሳኔ ማሳለፍ
2. የቁጥጥር ኮሚቴ ሪፖርት ማዳመጥና ውሳኔ ማሳለፍ
3. የ5 ዓመት ስትራቴጅክ እቅድ ዝግጅት ማዳመጥና ውሳኔ ማሳለፍ
4. የ2015 በጀት ዓመት እቅድ ዝግጅት ማዳመጥና ውሳኔ ማሳለፍ
5. በመተዳደሪያ ደንብና በብድር መመሪያው ላይ የማሻሻያ አንቀጾችን አዳምጦ ውሳኔ ማሳለፍ በሚሉት አጀንዳዎች ላይ ጉባኤተኛው ተወያይቶ ጠቃሚ ውሳኔዎችን አሳልፏል:: ከአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ማደራጃ የተወኩሉ አካላት በእለቱ ተገኝተው ለሸገር ጠቃሚ የሚሆኑ ሃሳቦችን ሰጥተዋል:: ሸገር እስከዚህ ወር ድረስ 47 ሚሊዮን ብር ካፒታልና 1832 አባላት አለው:: ይህ አፈፃፀም የአንድ ዓመት ከአምስት ወር ሥራ ውጤት ነው::

በጋራ እንችላለን!!!