Skip to content
ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/መሰ/የኅብረት ስራ ማህበር
መነሻ ገጽ
አባል ይሁኑ
አባል መሆን የሚችለው ማን ነው?
አባል ለመሆን የሚጠበቅ መስፈርት
ጥቅሞች
እንዴት አባል መሆን እንችላለን
የመረጃ ብሮሹር
ከእኛ ይበደሩ
መደበኛ ብድር
የመኪና ብድር
የቤት ብድር
ብድር ለማግኘት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
የብድር ማስሊያ
ከእኛ ጋር ይቆጥቡ
መደበኛ የተቀማጭ ሂሳብ
የህጻናት የተቀማጭ ሂሳብ
ለመኪና የሚቆጠብ
ለቤት የሚቆጠብ
የውስን ጊዜ ቁጠባ
ሸገር ገንዝብ ቁጠባና ብድር ማኅበር
ስለ እኛ
የኛ ቡድን
ያግኙን
ክፍት የሥራ ቦታዎች
ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/መሰ/የኅብረት ስራ ማህበርን ይፈልጉ
ምንጮች
በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቀዎች
ዜናዎች እና ኹነቶች
Toggle website search
Press Escape to close the search panel.
Menu
Close
መነሻ ገጽ
አባል ይሁኑ
አባል መሆን የሚችለው ማን ነው?
አባል ለመሆን የሚጠበቅ መስፈርት
ጥቅሞች
እንዴት አባል መሆን እንችላለን
የመረጃ ብሮሹር
ከእኛ ይበደሩ
መደበኛ ብድር
የመኪና ብድር
የቤት ብድር
ብድር ለማግኘት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
የብድር ማስሊያ
ከእኛ ጋር ይቆጥቡ
መደበኛ የተቀማጭ ሂሳብ
የህጻናት የተቀማጭ ሂሳብ
ለመኪና የሚቆጠብ
ለቤት የሚቆጠብ
የውስን ጊዜ ቁጠባ
ሸገር ገንዝብ ቁጠባና ብድር ማኅበር
ስለ እኛ
የኛ ቡድን
ያግኙን
ክፍት የሥራ ቦታዎች
ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/መሰ/የኅብረት ስራ ማህበርን ይፈልጉ
ምንጮች
በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቀዎች
ዜናዎች እና ኹነቶች
Toggle website search
Search this website
Information Broasher
Home
>
Information Broasher
ቁጠባ (Saving) ምን ማለት ነው? ቁጠባ በኢኮኖሚክስ ሳይንስ «የዛሬውን ፍጆታ ለነገው ተስፋና ኢንቨስትመንት ቆጥቦ የማሳደር ስልታዊ ውሳኔ» (Deferred Consumption) ሲሆን፤ በኢትዮጵያውያን ባህልና ታሪክ ደግሞ የክብር፣ የነጻነትና የህልውና መሰረት ነው። ታላቁ የኢኮኖሚክስ አባት አዳም ስሚዝ «አንድ ሰው የሚቆጥበው ሊያበለጽግ ከሚችለው የስራ እንቅስቃሴ ጋር ለማገናኘት ነው» እንዳለው ሁሉ፤ በታሪካችንም አያቶቻችን በክረምት ወራት የሚመጣውን አስቸጋሪ ጊዜ ለማለፍ በበጋው ወቅት እህልን በጎተራ አከማችተው «ስንቅ» ያዘጋጁ የነበረው ይህንኑ የቁጠባ ጥበብ በመተግበር ነበር። አባቶቻችን ከዕቁብ እስከ ዕድር የዘለቀውን የማህበራዊ ፋይናንስ ስርዓት ሲዘረጉ "የቆጠቡት ከረሃብ፣ የያዙት ከጥማት ይታደጋል " እያሉ ያስተማሩን፤ ቁጠባ የገቢ ማነስ ወይም የስስት መገለጫ ሳይሆን፣ የወደፊቱን አስቀድሞ የመመከትና የራስን የፋይናንስ ዕድል በራስ እጅ የመጻፍ የህይወት ጥበብ መሆኑን ለማሳየት ነው። ይህንን ጥንታዊ የጎተራና የዕቁብ የበረከት እሴት ከዘመናዊው የፋይናንስ ሳይንስ ጋር አጣጥሞ ለተግባራዊ ስኬት ማብቃት የዘመናችን ትልቅ የቢዝነስ ስልጣኔ ነው። በዚህች ዕለት በዕለተ ዓርብ፣ የወደፊት እቅድዎን ለመተለም ሲነሱ «ሳይቆጥቡ ማትረፍ፣ ሳይዘሩ ማጨድ አይቻለም» የሚለውን መመሪያ ልብ ይበሉ። የሸገር የቁጠባና ብድር አገልግሎት የቆየውን ባህላዊ እሴታችንን ከዘመናዊ፣ አስተማማኝና አትራፊ የፋይናንስ አማራጮች ጋር በማቀናጀት ለታላቁ ኢንቨስትመንትዎና ለስኬት ጉዞዎ ጠንካራ መደገፊያ ይሆንዎታል። ዛሬ በሸገር የቁጠባ ሂሳብዎ የሚያስቀምጧት ጥቂት ዘር የነገው ትልቅ የብልፅግና ፍሬ መነሻ ናትና፣ የቁጠባ ጉዞዎን ዛሬውኑ በሸገር የገንዘብ ቁ/ብ/ኃ/የተ/መሰ/ኅብረት ሥራ ማኅበር በመጀመር የነገዎን ስኬት ያረጋግጡ!
Time Value of Money)ምን ማለት ነው ? "ዛሬ የተዘራች ህያው ዘር፣ ነገ ከሚመኙት ካፖርት ትሞቃለች" (Time Value of Money) የቀደሙ አባቶቻችንና እናቶቻችን የፋይናንስንና የጊዜን ሚስጥር በቀመሮች ቢጽፉትም፣ በህይወት ልምዳቸውና በምሳሌያዊ አነጋገሮቻቸው ውስጥ የላቀ የኢኮኖሚ የላቀ ጥበብን አሳልፈውልናል። የገንዘብ በጊዜ ሂደት የሚኖረው እሴት (TVM) መሠረታዊ እውነት አባቶቻችን የዛሬዋ በእጅ ያለች አነስተኛ ነገር ነገ ከሚመኙት ያልተረጋገጠ ትልቅ ሀብት እንደምትበልጥ አስተምረውናል። በፋይናንስ ሳይንስም የዛሬዋ 100 ብር በጊዜ እና በወለድ አድጋ ትልቅ ሀብት የመሆን ህያው አቅም ስላላት፣ ከነገዋ ካልተረጋገጠች 1,000 ብር ትበልጣለች። ሸገር ለአባላቱ የሚያቀርበው ብድር አባላት የነገውን ሀብት ወደ ዛሬ እንዲያመጡ የሚያስችል የጊዜ ድልድይ ነው። አንድ አባል ማሽነሪ ወይም የንግድ ቦታ ለመግዛት 10 ዓመት ሙሉ መቆጠብ ቢኖርበት፣ የገበያ ግሽበት (Inflation) ገንዘቡን ይበላዋል። ሸገር ግን በብድር አማካኝነት የወደፊቱን የካፒታል አቅም ዛሬ በእጁ ላይ በማስቀመጥ፣ የጊዜን ውድመት (Loss of Purchasing Power) ወደ ምርታማነት ይቀይርለታል። አባላት ዛሬ ያስቀመጡት ገንዘብ ዝም ብሎ በካዝና ውስጥ ተቆልፎ እንዳይሞት፣ በሸገር በኩል ወደ ምርታማ ዘርፍ እንዲሰማራ በማድረግ የገንዘቡ የመግዛት አቅም በጊዜ ሂደት እንዳይደቅቅ ይከላከላል። የጊዜን እሴት የተገነዘበ አባል "ነገ እቆጥባለሁ" አይልም። የዛሬዋ 100 ብር ከነገዋ 1000 ብር የበለጠች ህያው ዘር መሆኗን ይረዳል:: "ሀብት ማለት በድንገት የሚመጣ ተአምር ሳይሆን፤ በጊዜና በህብረት የተሰራ የሳይንስና የትዕግስት ፍሬ ነው!" ሸገር የቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ተራ የገንዘብ ማከማቻ ሳይሆን፤ አባላቱ የጊዜን ወርቃማ ባህሪ በመጠቀም፣ በትንሽ ቁጠባ ተነስተው ትልቅ የሀብት ማማ ላይ እንዲወጡ የሚያስችል የፋይናንስ ጥበብ ትምህርት ቤት ነው። ውድ የሸገር አባላትና ሰራተኞች፣ ዛሬ የምናከናውነው እያንዳንዱ የፋይናንስ አገልግሎት የአባላቶቻችንን ህይወት በሳይንሳዊና በስልጡን መንገድ የሚገነባ መሆኑን በመገንዘብ፣ አዲሷን ቀን በታላቅ ተስፋና ጥራት እንድትጀምሩ እንመኛለን። ስኬታማና ቀን ይሁንላችሁ! ሸገር የገንዘብ ቁጠባ እና ብድርኃ/የተ/መሰ/ኅ/ስ/ማህበር በጋራ እንችላለን!!!
Members Login
News & Events
INFORMATION BROASHER
LOAN APPLICATION REQUIREMENT
LOAN CALCULATOR
FIND SHEGER SACCOS
Facebook
Telegram
Tiktok
youtube