Home
ራዕይ
በ2019 ዓ.ም በኢትዮጵያ መሪ የሆነ፣ ዲጅታል አገልግሎትን የሚጠቀም፣ የላቀ የፋይናንስአገልግሎት የሚሰጥ እና ተመራጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማኅበር መሆን ፡፡
ተልዕኮ
በህብረት ስራ ማህበራት መርህ የቁጠባን ባህል በማዳበር፣ አስተማማኝ ብድር በመስጠት እና ዘርፈ ብዙ ለውጥና እድገትን በመደገፍ የአባላትን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በጋራ መፍታት፡፡
መሪ ቃል
”በጋራ እንችላለን ”
“Together we can!!!”
እሴቶች
ቅንነት
ግልጽነት
ተጠያቂነት
አሳታፊነት
ማህበራዊ ሃላፊነት
ሌሎችን መንከባከብ
የቁጠባ አገልግሎት
መደበኛ የተቀማጭ ሂሳብ / ordinary Saving account
ሁሉም አባላት በህብረት ስራ ማኅበሩ ወስጥ አባል ሁነው እስከቀጠሉ ድረስ መደበኛ ቁጠባቸውን ማቋረጥ አይችሉም፡፡ የመደበኛ ቁጠባ መጠን በጠቅላላ ጉባኤ የተወሰነ ለሁሉም እኩል የሆነ 500 ብር ነው፡፡
ለመኪና የሚቆጠብ / Car Saving
መኪና መግዛት የሚፈልጉ አባሎቻችን የሚቆጥቡት የቁጠባ አይነት ነው፡፡ በዚህ ቁጠባ አንድ አባል እስከ 2 ሚሊዮን ብር ድረስ መበደር ይችላል፡፡
ለቤት የሚቆጠብ /home Saving
ቤት መግዛት የሚፈልጉ አባሎቻችን የሚቆጥቡት የቁጠባ አይነት ነው፡፡ በዚህ ቁጠባ አንድ አባል እስከ 3 ሚሊዮን ብር ድረስ መበደር ይችላል፡፡
የብድር አገልግሎት
መደበኛ ብድር/ Ordinary Loan
3/ሶስት ወር/ በተከታታይ የሚበደረውን 10 % መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ እና 5% እጣ የገዛ አባል መደበኛ ብድር የሚያገኝ ሲሆን የብድር ጣራው 120‚000.00 ሲሆን የመመለሻ ጊዜው እስከ 48 ወራት ድረስ ይሆናል፡፡
የቤት ብድር/ Home Loan
የቤት 16/አስራ ስድስት ወር/ በተከታታይ የሚበደረውን 15 % መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ እና 10% እጣ የገዛ አባል የቤት ብድር የሚያገኝ ሲሆን የብድር ጣራው 3‚000‚000.00 ሲሆን የመመለሻ ጊዜው እስከ 120 ወራት ድረስ ይሆናል፡፡
የመኪና ብድር/ Car Loan
የመኪና ብደር 12 - 16/አስራ ሁለት ወር እስከ አስር ስድስት ወር / በተከታታይ የሚበደረውን 20 % መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ እና 10% እጣ የገዛ አባል የመኪና ብድር የሚያገኝ ሲሆን የብድር ጣራው ከ 1,500,000.00 እስከ 2‚000‚000.00 ሲሆን የመመለሻ ጊዜው እስከ 120 ወራት ድረስ ይሆናል፡፡