Save With Us
መደበኛ የተቀማጭ ሂሳብ / ordinary Saving account
ሁሉም አባላት በህብረት ስራ ማኅበሩ ወስጥ አባል ሁነው እስከቀጠሉ ድረስ መደበኛ ቁጠባቸውን ማቋረጥ አይችሉም፡፡ የመደበኛ ቁጠባ መጠን በጠቅላላ ጉባኤ የተወሰነ ለሁሉም እኩል የሆነ 500 ብር ነው፡፡ለመደበኛ ቁጠባ 7% ወለድ ይታሰብለታል፡፡ በተከታታይ ሶስት ወር ያልቆጠበ በፈቃደኝነት እንደተሰናበተ ይቆጠራል፡፡ ይህ ቁጠባ ለብድር እንደ ቅድመቁጠባ ያገለግላል፡፡ ወጭ ሚሆነውም በጠቅላ ጉባኤ አባላቱ በሚወስኑት ወሳኔ ይሆናል፡፡
የህጻናት የተቀማጭ ሂሳብ / Child Account
ለህጻናት የሚቆጠብ የተሸለ ወለድ የሚታሰብለት
ለመኪና የሚቆጠብ / Car Saving
መኪና መግዛት የሚፈልጉ አባሎቻችን የሚቆጥቡት የቁጠባ አይነት ነው፡፡ በዚህ ቁጠባ አንድ አባል ከ1.5 እስከ 2 ሚሊዮን ብር ድረስ መበደር ይችላል፡፡ ብድሩንም ለማግኘት አባሉ የሚወስደውን የብድር መጠን 20% ሳይቆራረጥ መቆጠብና 10% ሸር መግዛት ይኖርበታል ወይም በአንድ ጊዜ መጀመሪያ ቆጥቦ ጊዜ ገደቡን ጠብቆ መበደር ይቻላል:: ለብድሩ ዋስትና የሚገዛው መኪና ይሆናል፡፡ ህብረት ስራ ማህበሩ በቂ ሀብት ካለዉ ከጊዜ ገደቡ ቀድሞ ሊያበድር ይችላል፡፡
ለቤት የሚቆጠብ /Home Saving
ቤት መግዛት የሚፈልጉ አባሎቻችን የሚቆጥቡት የቁጠባ አይነት ነው፡፡ በዚህ ቁጠባ አንድ አባል እስከ 3 ሚሊዮን ብር ድረስ መበደር ይችላል፡፡ ብድሩንም ለማግኘት አባሉ የሚወስደውን የብድር መጠን 15% ሳይቆራረጥ መቆጠብና 10% ሸር መግዛት ይኖርበታል ወይም በአንድ ጊዜ መጀመሪያ ቆጥቦ ጊዜ ገደቡን ጠብቆ መበደር ይቻላል:: ለብድሩ ዋስትና የሚገዛው ቤት ይሆናል፡፡ ህብረት ስራ ማህበሩ በቂ ሀብት ካለዉ ከጊዜ ገደቡ ቀድሞ ሊያበድር ይችላል፡፡
የውስን ጊዜ ቁጠባ እስከ አንድ አመት /Fixed Time Deposit up to one year
-ከብር 50,000.00 እስከ ብር 99,000.00 ከሆነ 10 %
-ከብር 100,000.00 እስከ ብር 199,000.00 ከሆነ 10.5 %
-ከብር 200,000.00 እስከ ብር 499,000.00 ከሆነ 11 %
-ከብር 500,000.00 እስከ ብር 999,000.00 ከሆነ 12 %
-ከብር 1000,000.00 እስከ ብር 1999,000.00 ከሆነ 13.5 %
-ከብር 2000,000.00 በላይ ከሆነ 14 % ይሆናል።
የውስን ጊዜ ቁጠባ እስከ ሁለት አመት እና ከዛ በላይ /Fixed Time Deposit up to two years and above
-ከብር 50,000.00 እስከ ብር 99,000.00 ከሆነ 11 %
-ከብር 100,000.00 እስከ ብር 199,000.00 ከሆነ 11.5 %
-ከብር 200,000.00 እስከ ብር 499,000.00 ከሆነ 12 %
-ከብር 500,000.00 እስከ ብር 999,000.00 ከሆነ 13 %
-ከብር 1000,000.00 እስከ ብር 1999,000.00 ከሆነ 13.75% -ከብር 2000,000.00 በላይ ከሆነ 14.5 % ይሆናል።